ehost expert review with uptime

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የጤና ባለሙያዎች ጥቅማጥቅሞች በክልሉ አንድ-ወጥ ያለመሆን፣ በአንድንድ ዞኖችና ወረዳዎች ከመመሪያ ውጪ የሚከናወኑ ተግበራት መኖራቸዉ ተገቢ አለመሆኑ እና ከዚህ በፊት በወጣው የስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰድ መመሪያ መሠረት የጤና ባለሙያዎች ኬሪየር ስትራክቸር እንደቀድሞዉ እየተሰራ እንዲቆይና ፐብሊክ ሰርቨስ ቢሮ ጉዳዩን ለሚመለከተዉ አካል አቅርቦ ምላሽ እየተጠባበቀ በመሆኑ የጤና ባለሙያዎች እንደወትሮዉ የጤና ስነ-ምግባራቸውን በመጠበቅ ህብረተሰቡን በታማኝነት እያገለገሉ መቆየት እንደሚገባቸዉ አሳስበዋል፡፡
አያይዘው የጤና ኤክስቴንሽን ዝውውርና የሰራተኞች ቅጥርና ምደባ እንዲሁም የሐኪሞች ምደባ ግልጽ በሆነ አሰራር ተደግፎ ካልተሰራ በሀገሪቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ ጥያቄ እያስነሳ የሚቀጥል በመሆኑ ቢሮዉ ወጥነት በሌላቸዉ አሰራሮች ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንዳለና በትዉዉቅ፣ በዝምድናና የበላይ አካል ትዕዛዝን ተቀብሎ በመፈጸም የሚፈጠሩ አድሎአዊ አሰራሮች ላይ ተከታታይነት ያለዉ እርምጃ እንደሚወሰድም ጠቁመዋል፡፡ 
በዚሁ ወቅት አንዳንድ ታሳታፊዎች እንደገለጹት የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የኬሪየር ስትራክቸር አሰራር በክልላችን ውስጥ አንድንድ ዞኖችና ወረዳዎች በአንድ እርከን ሲሰሩ ሌሎች ደግሞ በደረጃ መሰራቱ ፤የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ዝውውር ቢፈቀድላቸውም ፍትሐዊነት በጎደለዉ መልክ ዝውውር መሰጠቱ ፤የሐኪሞች ምደባ በአንድንድ ዞኖች ላይ ለአከባቢ ሰው ክፍት ቦታ አለ መባሉና አንዳንድ የበላይ አመራር አካላት ዝውውር ቅጥርና ምደባ በመመሪያና ደንብ ሳይሆን በትዕዛዝ እንዲፈጸም ማድረጋቸው የመልካም አስተዳደር ችግሩ ዋነኛ መንስኤ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ከዙሁ ጋር በተያያዘ የክልል ጤና ቢሮ ሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ባለሙያ አቶ ደርሞሎ ቀድራላህ እንደገለጹት በጤና ሳይንስ በኮለጅ ላይ ለሚያስተምሩ የጤና ባለሙያዎችም ሆነ ሌሎች የጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን ጥቅማ ጥቅማቸው ለማስከበር በቅድሚያ የመተዳደሪያ ደንብ መጽደቅ እንዳለበትና የኮሌጅ መተዳደሪያ ደንብ ለማጽደቅ የኮሌጅ መዋቅር በደቡብ ክልል ጤና ቢሮና ፐብሊክ ሰርቨስና ሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ቢሮ በኩል እየተጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡ 
የፐብሊክ ሰርቨስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ መኮንን በማጠቃለያቸዉ የጤና ባለሙያዎች ኬሪየር ስትራክቸርን የተመለከተ ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚነሳ ቢሆንም እንደ ሀገር ያለመመሪያና ደንብ መክፈላቸው አግባብነት የሌለዉ ስራ በመሆኑ በሀገርቱ ላይ ችግር መፍጠሩን ተናግረዉ አዲሱ የአሰራር አዋጅ ተግባራዊ እስከሚሆን ድረስ ከዚህ በፊት ያለውን መመሪያና ደንብ ተከትሎ መስራት አስገዳጅ መሆኑን ጠቁመዉ ያለምንም መመሪያ ጥቅሙን የሰጠ አካል ተጠያቂ ስለሆነ ፈጻሚዉ ራሱን ከችግር የሚያፀዳ ስራ መስራትና የተሰጠዉን ሃላፊነት በተጠያቂነት መወጣት እንደሚገባዉ አሳስበዋል፡፡