ehost expert review with uptime

ከደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ለ2012 የትምህርት ጊዜ መጠቀሚያ የሚውል የሚሆን የትምህርት መገልገያ የተገዙ ቁሳቁሶችን አስረክበዋል፡፡ ይኸው ድጋፍና ክትትል በማድረግ የሁሉንም የህብረተሰብ ተሳትፎ እና ርብርብ በወሳኝ መልኩ የሚፈልግ መሆኑ ተገልጾዋል፡፡ቤዛ ለትውልድ የአካል ጉዳተኛ ስልጠናና ትምህርት ክፍል የቦርዱ ሳብሳቢ አቶ ፀሐይነህ አዳም ባስተላለፉት መልዕክት የወደቁትን የህብረተሰብ ክፍልን አንስቶ መርዳት ከሁሉም ሕብረተሰብ ክፍል የሚጠበቅ ስለሆነ ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ በመሆኑ እነዚህን የአዕምሮ ውስንነት ያለባቸው፣ መስማት እና ማየት የተሳናቸውን እና እንዲሁም ወላጅ አጥ ሕፃናትና ወጣቶች በድርብ ችግር መውደቃቸው አሳዛኝ በመሆኑ እንደጉዳታቸው ተለይተው ቁሳቁሶች ቢሰጣቸው መልካም መሆኑ በመግለጽ ለወገን ደራሽ ወገን ስለሆነ የሁሉም ሕብረተሰብ ድጋፍና ዕርዳት ይሻናል በማለት ገልጸዋል፡፡ ፍቅር በሕይወት ወጣቶችና ሕፃናት አካል ጉዳተኞች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አብርሃም ማሩ እንደገለጹት ይህ ማህበር 1998 ዓ/ም ጀምሮ ለ13 ዓመታት የበርካታ ወላጅ አጥ ወጣቶችና ሕፃናት ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ስነልቦናዊ ችግሮቻቸውን በመረዳት ለተከታታይ 13 ዓመታት እየሰራ ያለ ማህበር በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት 45 ሴቶችንና 25 ወንዶችን በአጠቃላይ 70 ሕፃናትና ወጣቶችን እያስተማረ ስለሚገኝ እነዚህ ወጣቶች የተሻለ ሕይወት እንዲመሩና ቤተሰቦቻቸውን እንዲረዱ የሁሉም ህብረተሰብ እርዳታ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ አያይዘውም ማህበራችን በክልላችን በ10 ዞኖችና በ3 ልዩ ወረዳዎች እንዲሁም በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ስለሚገኝ ማህበራችንን ለማጠናከርና ወገኖቻችን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በዘላቂነት የሁሉም ተሳትፎ እንደሚያስፈልጋቸው አሳስበዋል፡፡ ከሚረዱት ተማሪዎች መካከል አንድንዶቹ ከክልሉ ጤና ቢሮ ለተበረከተላቸው የትምህርት ቁሳቁስ መረከባቸው ያስደሰታቸው ቢሆንም ይህ ቁሳቁስ በዓመት ሁለት ግዜ ለሚያስፈልጋቸው የደብተር እና እስክሪብቶ ጤና ቢሮ ብቻ ሳይሆን እኛ ወላጅ አጥነታችንን በማሰብ የሁሉም ህብረተሰብ ክፍል ለእኛ መራራትና ርብርብ ማድረግ የሚያስፈልገው በመሆኑና ለሴቶች ደግሞ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፤ ቅባቶችና ቅያሪ አልባሳት የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ የወላጅነት ፍቅሩን በመግለጽ ወላጅ እንዲሆናቸው ጠይቀዋል፡፡