ehost expert review with uptime


በተያያዘ መልኩ በአሁኑ ሰዓት የወባ በሽታ በመከላከል ረገድ ወደ ማስወገድ ደረጃ ለመድረስ እየተሰራ ያለ ዘርፈ ብዙ ስራ ያለ ቢሆንም በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የወባ በሽታ እየጨመረ መሆኑ የሚድያ አካላትና የጤና ባለሙያ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በጋራ በመቀናጀት ህብረተሰባችን በጎናችን በማሰለፍ ከዚህ ቀደም የነበረውን መጠነሰፊ ርብርብና ተነሳሽነት በመድገም በሽታውን ሙሉበሙሉ ከክልላችን ማስወገድ እስከሚቻልበት ደረጃ ድረስ መንቀሳቀስ እንደሚገባን አሳስበዋል፡፡
የከልል ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት ምላሽ የስራ ሂደት ባለሙያ አቶ አባተ አዶሳ በበኩላቸው ኮሌራ በሽታ ምንም ህመም የሌለው የሚያስመልሰው የሩዝ ሾርባ የሚመስል ፈሳሽ ትውከትና ምንም ቁርጠት የሌለው የማያቋርጥ ተቅማጥ ምልክቶቹ እንደሆነና በሽታው በተከሰተ ሰዓት ወዲያውኑ ወደ ጤና ተቋማት በመውሰድ እንዲታከሙ በማድረግ ማንኛውንም ፈሳሽ ቶሎ ቶሎ መውሰድና ኮሌራ ተላላፊ በሽታ በመሆኑ ከንክኪ ራሳችንን መከላከል እንደሚገባን በመግለጽ አስቀድመን ለመከላከል በክልላችን በሽታው በይከሰትም ለህብረተሰቡ ጠንካራና ፈጣን እንዲሁም ግልጽና በማያሻማ መልኩ መረጃ መስጠት እንዲሁም ውሃን ማከም፤ ምግብን አብስሎ፤ የአከባቢና የግል ንጽህና መጠበቅና መሰል ንጽና መጠበቅ መከላከያ መንገዶቹ በመሆናቸው በተከታታይ ማስተማር እንደሚገባ አንስተው አቶ በለጠ በበኩላቸው የወባ ስርጭት በአንዳንድ አካባባቢዎች ከዚህ ቀደም ከፍ ማለቱ አሳሳቢ ስለሆነ ጤና ባለሙያዎች፣ ሚድያ አካላትና ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የመከላከል ስራውን በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
ከቤቱ ተሳታፊዎች አንዳንዶቹ የኮሌራ በሽታ የክልላችንን ህዝብ እንዳያጠቃ በአገራችን ሌሎች አካባቢዎች የተከሰተው ወረርሽኝ ወደ ክልሉ እንዳይዛመትና እናቶችና ህፃናትን እንዳያጠቃ በሴቶች አደራጃጀት ላይ በትኩረት ቢሰራ መልካም እንደሆነ አንስተው የወባም በሽታ ነፍሰ ጡር እናትና ህጻናት በፍጥነት ስለሚያጠቃ ህብረተሰቡን አስቀድሞ ለማስጠንቀቅ የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ ላይ የጤና ባለሙያዎች፣ የሚድያ አካላት እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች እንደነበሩ ታውቋል ፡፡