ehost expert review with uptime

በዚሁ ወቅት የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሃጂ ኑርዬ ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት ከመኪና ፍሰት የፀዱ መንገዶች ቀንን እንዲሁም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር በዶ/ር አብይ አህመድ የተያዘውን ከተሞቻንን በጋራ ማጽዳት ግብ በማሳካት ህብረተሰቡ የራሱን ጤና እራሱ እንዲጠብቅ የሚያስችል በመሆኑ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ለጤናማ ህይወት በመከተል የግልና የአከባቢ ንጽህና መጠበቅ ልምዱን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባውም ተናግረዋል፡፡

በዚህ ወቅት ከተሳታፊዎች አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት እንደገለጹት ከተማዋን ንጹህ፤ ጽዱና ለስራም ሆነ ለጤና ተስማሚ በማድረግ ተግባር የህብረተሰቡ ተነሳሽ ነት፤ ተሳትፎና እና ድጋፍ የላቀ መሆኑን ተናግረው በእለቱ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ከተሽከርካሪ ፍሰት ነፃ የሆኑ መንገዶች ቀን የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለጤና ጅምሩ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ በንግግራቸው መሰል ተግባራት በዘመቻ ብቻ የታጠሩ እንዳይሆኑና ህብረተሰቡ ባህሉ አድርጎ በየእለት ተእለት እንቅስቃሴው እንዲያጠናክራቸውና ጤናውን እንዲጠብቅ ለማስቻል ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በህብረተሰቡ ጤና ላይ እያስከተሏቸው ያለውን ጉዳቶችን ጨምሮ ከደረቅና ከፈሳሽ ቆሻሻዎች አያያዝና አወጋገድ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ተከታታይነት ያላቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን መስራት እደሚገባ ተናግረዋል ፡፡