ehost expert review with uptime

ላይ የተስተዋሉ የግብአት አቅርቦት ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ የሚሹ በመሆናቸዉ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ይበልጥ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል::
በክልሉ የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተሰራዉ የተጠናከረ ስራ አመርቂ ዉጤት ማስመዝገብ የተቻለ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት አጎበርን በወቅቱና በሚፈለገዉ ብዛት በማሟላት እና የኬሚካል ርጭቱን ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ከማድረግ አኳያ ለታየዉ ክፍተት አፋጣኝ ምላሽ ካልተሰጠዉ የወባ በሽታ በክልሉ ስጋት ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል::
በመጨረሻም ከድንገተኛ ጤናና ጤና ነክ አደጋዎች ጋር በተያያዘ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚከሰተዉ ችግር በቂ ድጋፍ አለማድረግ፣ በሆስፒታሎች ዉስጥ የአንቡላንስ እና የተሽከርካሪ እጥረት እንዲሁም ሌሎች ግብአቶች እጥረት እንደ ክፍተት ተይዞ ሊሰራበት እንደሚገባ፣ ለድጋፋዊ ክትትሉ አባላት አሳስበዋል::