ehost expert review with uptime

በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል በተለያዩ የጤናው ዘርፍ አጀንዳዎች ላይ ሲመክር የቆየው 21ኛው ዓመታዊ ገባኤ ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ከዘጠኙ ክልሎችና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ፤ ከጤና ሚኒስቴር፤ ከተጠሪ ተቋማትና አጋር ድርጅቶች የተውጣጡ በድምሩ ከ900 በላይ ተሳታፊዎችን ለአራት ቀናት ያስተናገደው ገባኤው በተለይም ባለፉት ሁለት ቀናት በቡድን ውይይት በመሳተፍ ለቀጣይ ስራ አጋዥ የሆኑ ነጥቦችን አንስተዋል፡፡ በሰባት ቡድኖች ተከፋፍለው የተወያዩት ተሳታፊዎች በተለይ በወረዳ ትራንስፎርሜሽን፤በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም የጥናት ውጤት፤ በሁለተኛው የጤናው ዘርፍ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ፤በአዕምሮ ጤና፤ በቲቢ፤በቆላ በሽታዎች፤በክትባት፤ ያገባኛል /I-CARE/ እና ሌሎችም ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት በቀጣይ ለሚከናወኑ ተግባራት ስንቅ የሚሆኑ ነጥቦች ተገኝተዋል፡፡

አቶ አቅናው ካውዛ የደ/ብ/ብ/ህ/ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊና በጤና ቢሮው የህክምና አገልግሎቶች ሃላፊ አቶ ዩሃንስ ላታሞ የጥቅምት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ሃገር አቀፍ የደም ልገሳን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ በስካይላይት ሆቴል በጋራ ሰጥተዋል፡፡

21ኛው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ የምክክር ጉባኤ ላይ ከተለያዩ ክልሎች በተለያዩ የጤና ዘርፎች በአፈጻጸማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የጤና ባለሙያዎች፣ የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተሸላሚ የሆኑ ሲሆን